Demoz paydemoz.com

ለኢትዮጵያ ድርጅቶች የደመወዝና የሰው ሀብት ሥርዓት

የገቢ ግብርና ጡረታ በአዲሱ ሕግ መሠረት ይሰላሉ፤ የደመወዝ ደረሰኝ በአማርኛ ወይም በእንግሊዝኛ ይወጣል፤ ፈቃድ፣ የሥራ ሰዓትና የቅጥር ውሎችም በአንድ ቦታ ይያዛሉ።

የናሙና ደመወዝ ደረሰኝሐና ግርማ፣ ሒሳብ ሠራተኛ
መስከረም 2019
መሰረታዊ ደመወዝ
15,000.00
የገቢ ግብርየ35% ምጣኔ፣ ተቀናሽ 2,050 ብር
−3,200.00
ጡረታ፣ 7%የሠራተኛው ድርሻ
−1,050.00
የተጣራ ክፍያ
10,750.00
የድርጅቱ የጡረታ መዋጮ፣ 11%
1,650.00

በብር። የግብር ምጣኔዎቹ ከአዋጅ ቁጥር 1395/2017 ናቸው። ትክክለኛ ደረሰኞች አበሎችን፣ የትርፍ ሰዓት ክፍያንና ሌሎች ተቀናሾችንም ያሳያሉ።

የአንድ ወር ደመወዝ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ

  1. የሥራ ሰዓትና ፈቃድን መዝጋትከስልክ፣ ከቢሮ ወይም ከጣት አሻራ ማሽን የተመዘገቡ መግቢያ መውጫዎችና የጸደቁ ፈቃዶች ወደ ወሩ ይገባሉ።
  2. ደመወዝ ማስላትየትርፍ ሰዓት፣ መቅረት፣ አበል፣ ብድርና ቅድሚያ ክፍያ ይቆጠራሉ፤ ግብርና ጡረታ ለእያንዳንዱ ሠራተኛ ይሰላሉ።
  3. መፈተሽና ማጽደቅማንም ከመከፈሉ በፊት ገምጋሚው ድምሩን አይቶ ያጸድቃል።
  4. መክፈልና ሪፖርት ማድረግየባንክ ደብዳቤ፣ የገቢ ግብርና የጡረታ ፋይሎች ይወርዳሉ። ሠራተኞች ደረሰኛቸውን በፖርታሉና በቴሌግራም ያያሉ።

ሌላው የሰው ሀብት ሥራም በዚያው ቦታ

ሠራተኞችየሠራተኞች መዝገብ፣ ሰነዶችና የመታወቂያ ፎቶ፣ የሥራ ክፍሎችና ቅርንጫፎች
ሰዓትና ፈቃድበስልክ፣ በቢሮ ወይም በጣት አሻራ ማሽን የሥራ ሰዓት፤ ፈረቃ፣ ፈቃድ፣ በዓላት
ቅጥርና ውልየሥራ ማስታወቂያና ኦንላይን ማመልከቻ፣ የሲቪ ማጣሪያ፣ የቅጥር ውል
ዕድገትና ሥልጠናየሥራ አፈጻጸም ግምገማ፣ ሥልጠና፣ ምዘና
ገንዘብና ንብረትየወጪ ጥያቄ፣ የደመወዝ ቅድሚያ ክፍያ፣ የድርጅት ንብረት
ስንብትበሕጉ የማስጠንቀቂያ ጊዜ የሚፈጸም ስንብት፣ ክሊራንስ
ደንብና ጥራትየማስጠንቀቂያ ደብዳቤ፣ የሕግ ተገዢነት ማስታወሻ፣ የደንበኞች አስተያየት
መሣሪያዎችደብዳቤና የሥራ ማስታወቂያ ለመጻፍ እገዛ፣ የአሠሪና ሠራተኛ ሕግ መመሪያ

ለኢትዮጵያ ሕግና ቋንቋ የተሰራ

  • የገቢ ግብር፦ በአዋጅ ቁጥር 1395/2017 የተቀመጡት ስድስቱ ወርሃዊ ምጣኔዎች
  • ጡረታ፦ 7% ከሠራተኛው፣ 11% ከድርጅቱ
  • የሠራተኛ ሕግ፦ የትርፍ ሰዓት፣ ፈቃድና ማስጠንቀቂያ በአዋጅ ቁጥር 1156/2011
  • ዘመን አቆጣጠር፦ የክፍያ ወራት ከመስከረም እስከ ጳጉሜ
  • ቋንቋ፦ ገጾችና ደረሰኞች በአማርኛ ወይም በእንግሊዝኛ

ደመወዝ ሚስጥር ሆኖ ይቆያል

  • ደኅንነቱ በኢመደአ (INSA) ኦዲት ተደርጓል
  • ለባለቤቶች ባለሁለት ደረጃ መግቢያ
  • ደመወዝ ማን እንደሚያይ ሚናዎች ይወስናሉ
  • እያንዳንዱ ለውጥ በእንቅስቃሴ ታሪክ ውስጥ ይቀመጣል